በፍፁም! መጠቀም ያለብሽ ለሁሉም ሰው የሚመከረውን የእንክብል መጠን ብቻ ነው ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የሰውነት ክብደት ወይም ከፍተኛ የውፍረት መጠን የመድሀኒቶቹን ስኬታማነት እንደማይቀንሰው ነው፡፡ ስለዚህ ተጨማሪ እንክብሎች ወይም የእንክብል መጠን መውሰድ አይኖርብሽም፡፡
ስለ ውርጃ እንክብሎች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የውርጃ እንክብሎች አይነትና ጥቅማቸው
እርግዝናሽ መንታ እንደሆነ ብታውቂ እንኳን የእንክብሎቹ የአወሳሰድ መጠን አይቀየርም፡፡ ለመንታ እርግዝና የምትጠቀሚው የአወሳሰድ መጠን ከሌ ላው ጊዜ የተለየ አይሆንም፡፡ የእንክብል መመሪያዎች ለመንታ እንዲሁም ለነጠላ እርግዝና ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡
በጭራሽ! ሁሉም እርግዝና የተለየ ክስተት ነው፡፡ ምን አልባት ከዚ በፊት የውርጃ እንክብል ተጠቅመሽ ከነበረ አሁን በድጋሜ ለሆነው ላልተፈለገ እርግዝና ከመደበኛው ተጨማሪ መጠን ያለው እንክብል መውሰድ አይኖርብሽም፡፡
በማህፀንሽ ውስጥ የእርግዝና መከላከያ መሳሪያ ካለ (ለምሳሌ፣ ኮፐር አይዩዲ ወይም የፕሮጄስትሮን አይዩዲ) የጽንስ ማስወረድ እንክብሎችን ከመዉሰድሽ በፊት እነዚህን ከማህጸን ማስወጣት በከፍተኛ ደረጃ ይመከራል፡፡
ከክኒኖች ጋር ውርጃ ሲያደርጉ እንደተለመደው ጡት ማጥባት ይችላሉ። ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ወደ ጡት ወተት የሚገቡት በጣም ትንሽ በሆኑ መጠኖች ነዉ፣ እና እነዚህ መጠኖች በአንቺ ጨቅላ ህጻን ላይ የጎንዮሽ ችግሮች ወይም ጉዳቶች አይፈጥሩም፡፡ እንክብሎችን በመጠቀም ጽንስ ማስወረድ ሂደት ላይ ጡት ማጥባት ሳይስተጓጎል መቀጠል ይችላል፡፡
ከ HIV ጋር እምትኖሪ ከሆነ፣ አንቺ ልክ እንደማንኛዉም ሴት እንክብሎችን በመጠቀም ጽንስ ማስወረድ ትችያለሽ፡፡ ለተሻለ ጤንነት አንታይሬትሮቫይራል መድሀኒቶችን መጠቀምሽ ሁልጊዜም ቢሆን የሚመከር ነዉ፡፡