እኛ ማን ነን እና የዚህ ፓሊሲ ይዘት መጠን፡

HowToUseAbortionPill (ድርጅቱ ወይም እኛ) ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማስወረድን በተመለከተ ትክክለኛ እና በጥንቃቄ የተዘጋጀ መረጃን በዌብሳይት እና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሰዎች ለማድረስ ዲጂታል ስርዓቶችን የሚያቀርብ፣ በዚህም አማካኝነት ሰዎች በራሳቸዉ ፍላጎት ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማስወረድ የሚያስችላቸዉ(ስርዓቱ) ፣ለትርፍ-ያልተቋቋመ ድርጅት ነዉ፡፡ ስርዓቱ ስለ ተጠቃሚዎቹ በግለሰብ ደረጃ ተለይቶ መታወቅ የሚችል መረጃን (ፒአይአይ)ይሰበስባል፣ ይህም የድርጅቱን ሰራተኞች፣ ፍሪላንሰሮች፣ እና የስራ ቅጥር አመልካቾችን(ተጠቃሚዎች) መረጃን ያካትታል፡፡ ይህ የግላዊነት ፓሊሲ እኛ የምንሰበስባቸዉን ፒአይአይ እና የእነርሱን ፒአይአይ በተመለከተ የተጠቃሚዎችን መብቶች ይዘረዝራል፡፡ ምንም እንኳን እኛ በርካታ የስርዓቱን ገጽታዎች ብንቆጣጠርም፣ የተወሰኑ ክፍሎች ዉጤታማነቱን ለማጎልበት ሲባል ከድርጅቱ ዉጪ በሆኑ የአገልግሎት አቅራቢዎች አማካኝነት የሚቀርቡ ናቸዉ፡፡
ይህ የግላዊነት ፓሊሲ የተቋቋመዉ የተጠቃሚዎችን ግላዊነት ለመጠበቅ ነዉ፡፡

በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ ላይ የተደረጉ ለዉጦች እና ተጨማሪ የግላዊነት ማሳወቂያዎች

የእኛ ይህን የግላዊነት ፓሊሲ ወደፊት የማሻሻል መብታችን የተጠበቀ ነዉ፡፡ እኛ የተጠቃሚዎችን ግላዊነት ላይ ጉልህ ተእጽኖ የማያሳድሩ አነስተኛ የሆኑ ለዉጦች ስናደርግ ለተጠቃሚዎችን አናሳዉቅም – እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ የተሻለ የግላዊነት ከለላልን ማቅረብ፣ የጽሁፍ ስህተቶችን ስናርም፣ ወይም የማሟያ መረጃዎችን በምንጨምርበት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛዉም ጉልህ የሆነ ለዉጥ፣ እኛ ተጠቃሚዎችን በኢሜይል አድራሻቸዉ አማካኝነት የምናሳዉቃቸዉ ይሆናል፡፡ ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል የኢሜይል አድራሻ የማይኖራቸዉ ከሆነ፣ እኛ ስለ ማንኛዉም የፓሊሲ ለዉጦች ልናሳዉቃቸዉ አንችልም፡፡ ይህ የግላዊነት ፓሊሲ ለወደፊት እንዲዘምን ሊደረግ ወይም ከእኛ ጋር ለሚኖሩ የተለዩ ግንኙነቶች ጠቃሚ የሆኑ አዲስ ስሪቶች ወይም ተጨማሪ የግላዊነት ማሳወቂያዎች ማሟያዎች ሊደረጉበት ይችላል፡፡ እነዚህ ማሳወቂያዎች በዚህ ፓሊሲ ዉስጥ ሊካተቱ፣ በድርጅቱ ዌብሳይት ላይ ሊለጠፉ፣ እና/ወይም እርስዎ እንዲያገኙዎቸዉ በተናጠል ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

ወደ ሶስተኛ- ወገን ዌብሳይቶች የሚወስዱ ማስፈንጠሪያዎች

የዚህ የግላዊነት ፓሊሲ ይዘት ማስፈንጠሪያዎችን ሊጠቀሙ የሚችሉ ወይም በስርዓቱ በኩል ማግኘት የሚቻሉ ሶስተኛ- ወገን ዌብሳይቶች ላይ የሚሳራ አይሆንም፡፡ እኛ ይህን መሰል ማስፈንጠሪያዎችን ለሚጠቀሙ ዌብሳይቶች ወይም አገልግሎቶች ይዘት፣ ገጽታዎች፣ ተግባራዊነት፣ ወይም የግላዊነት ልምምዶች ተጠያቂነት የለብንም፡፡ የማንኛዉም ማስፈንጠሪያዎችን የሚጠቀሙ ዌብሳይቶች መረጃ መሰብሰብ እና ጥቅም ላይ ማዋል በእነዚህ አካሎች የግላዊነት ማሳወቂያ፣ መግለጫ፣ ወይም ፓሊሲ የሚመሩ ይሆናል፡፡ እኛ የተጠቀሱትን መረጃዎች እንዲያነብዋቸዉ እናበረታታዎታለን፡፡

የተሰበሰበ በግለሰብ ደረጃ ተለይቶ መታወቅ የሚችል መረጃ፡

በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ ዉስጥ፣ ሁሉም በግለሰብ ደረጃ ተለይቶ መታወቅ የሚችል መረጃ በአንድነት “ፒአይአይ” በመባል ይጠራል፡፡ እኛ ሰፊ መጠን ያላቸዉ ፒአይአይ፣ በተጠቃሚዉ እና በሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ከተጠቃሚዎች እና ስለ ተጠቃሚዎች እንሰበስባለን፡፡ ስለሆነም፣ ፒአይአይ እነዚህን ሊያካትት ይችላል፡

  • ስም
  • የኢሜይል አድራሻ
  • የስልክ ቁጥር
  • አይፒ አድራሻ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ፣ የማሰሻ አይነት፣ እና ቋንቋ
  • አድራሻ
  • የጊዜ ክልል
  • ጥቅም ላይ የዋሉ ቋንቋዎች
  • እድሜ፣ ጾታ፣ የግል ፎቶዎች፣ እና ተጠቃሚዎች የሚሰጡዋቸዉ ሌሎች የግል መረጃዎች
  • ተጠቃሚዎች ስለ ጤናቸዉ፣ የመራቢያ/እርግዝና ጉዳዮች፣ ከስርዓቱ ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች ምክንያት፣ እና ለእነርሱ የመራቢያ ጤና እንክብካቤ አገልግሎቶች ማግኘት እና ክፍያ መፈጸም መቻል በሚመለከት የሚሰጡዋቸዉ መረጃዎች፡፡
  • የስራ ቅጥር ሁኔታ እና የቀጣሪ መረጃ
  • የስርዓቱን የትኛዉንም ገጽታ በሚመለከት የሚሰጡ ምስክርነቶች እና ደረጃ ምደባዎች.

የእርስዎን የግል መረጃዎች መሰብሰብ፡

እኛ ፒአይአይ መሰብሰብ ከመጀመራችን በፊት ፍቃድ ለማግኘት እንሰራለን፡፡ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ተጠቃሚዎች ለሁለቱም (1) የዚህን ግላዊነት ፓሊሲ ዉሎች እና (2) የእኛን እነርሱ የሚሰጡዋቸዉ መረጃዎች መሰብሰብ፣ መጠቀም፣ እና ማከማቸት እንዲሁም ከእነርሱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ስርዓቱ ለሚሰበስበዉ መረጃ ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ ቃላቶች ለመግለጽ፣ ተጠቃሚ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት በሚፈጥርበት ጊዜ ላይ፣ ስርዓቱ ወዲያዉኑ ተጠቃሚዉ ከሚጠቀመዉ ቴክኖሎጂ ፒአይአይ ይሰበስባል እና በማንኛዉም ይህን መሰሉ ከስርዓቱ ጋር በሚደረግ ግንኙነት ወቅት ተጠቃሚዉ የሚሰጣቸዉ ፒአይአይ የሚሰበስብ ይሆናል፡፡
ለግላዊ መረጃ አሰባሰብ ተግባራዊ የሚደረጉ ዘዴዎች፡

  • በተጠቃሚዉ በፍቃደኝነት የሚደረጉ አስተዋጽኦዎች፤
  • የተጠቃሚዎች ከስርዓቱ ጋር የሚደረግ ግንኙነቶች፣ ይህም ሶስተኛ ወገን/ ከድርጅቱ ዉጪ የሆኑ አገልግሎት አቅራቢዎችን ያካትታል፡፡
  • ከተጠቃሚዎች ጋር የሚደረግ ዉይይቶች፡፡

እኛ ያለማቋረጥ ዉጤታማ፣ ደህንነታቸዉ የተጠበቁ ዘዴዎችን ለ ፒአይአይ መሰብሰቢያነት ለማግኘት እንሰራለን፣ እና አዲስ ዘዴዎችን ስንጠቀም ሁኔታዉን ለማሳወቅ እኛ ይህን የግላዊነት ፓሊሲ የምናዘምን ይሆናል፡፡

እኛ የእርስዎን የግል መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ እናዉላለን፡

እኛ የምንሰበስበዉን እና/ወይም ሰብስበን የያዝናቸዉን ፒአይአይ መረጃዎች በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ እናዉላለን፡

  • ከእርስዎ ጋር እንደ ተጠቃሚ ግንኙነት ለመፍጠር ይህም የሚያካትተዉ ነገር ግን በዚህ አይገደብም ከእርስዎ የመራቢያ አማራጮች ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ተዛማጅ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን ለማቅረብ፡፡
  • እኛ የምናቀርባቸዉን አገልግሎቶች፣ ምርቶች፣ እና እሴቶች ለማሻሻል እና/ወይም ለተጠቃሚዎች እና ለሌሎች ይህን መሰሉ ማሻሻያዎችን እና ተያያዥ መረጃዎችን ለማስረዳት፡፡
  • ለስርዓቱ አስተዳደራዊ ተግባራቶችን ማከናወን እና/ወይም በመደበኛ የስራ ቅጥር እና በድርጅቱ ክንዉኖች ሂደት ላይ፡፡
  • በድርጅቱ እና/ወይም ለድርጅቱ ምርምሮችን ማከናወን፡፡
  • ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በትብብር ለምንሰጣቸዉ የተወሰኑ የድረ ገጽ ትምህርት ኮርሶች፣ እኛ ለሌላኛዉ ድርጅት በእነዚህ የድረ ገጽ ትምህርት ኮርሶች ከሚሳተፉ የእነርሱ አባላቶች ከሰበሰብነዉ የተወሰኑ ፒአይአይ እንሰጣለን፡፡
  • የገቢ ማሰባሰቢያ ጥረቶች፣ ይህም ለድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ ለሚያደርጉ ወይም ሊያደርጉ የሚችሉ ድርጅቶች የፒአይአይ ማጠቃለያዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡
  • ለሕግ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የመንግስት ኤጀንሲዎች ወይም ባለስልጣኖች፣ ወይም በሕግ በተፈለገዉ መልኩ ለሶስተኛ ወገኖች፣ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣ የፍርድ ቤት መጥሪያ፣ ወይም በድርጅቱ ለሚደረግ የሕግ ሂደቶች ፒአይአይ ማቅረብ፡፡

እኛ የእርስዎን ፒአይአይ ማግኘት እንዲችል ለሚጠይቅ የትኛዉም የመንግስት አካል ወይም ሶስተኛ-ወገን ፒአይአይ ይፋ እንድናደርግ ግፊት እንዳደረግብን ምክንያታዊ የሆኑ እና ሕጋዊ እርምጃዎችን የምንወስድ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን፣ የእኛን ድርጅት የመሰሉ አካሎችን ለማስገደድ ሕጋዊ መብት ያላቸዉ የመንግስት አካሎች እና/ወይም ሶስተኛ- ወገኖች ሊኖሩ የሚችሉባቸዉ ሁኔታዎች ይኖራሉ፤ እናም፣ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ፣ የእኛ ድርጅት ትብብር ማድረግ ሊኖርበት ይችላል፡፡
በስርዓቱ ዉስጥ ተሳታፊ በሚሆኑ ሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች አማካኝነት ለተሰበሰቡ እና/ወይም ለተጠራቀሙ ፒአይአይ፣ እኛ የእነርሱ ይህን መሰሉ ፒአይአይ ጥቅም ላይ ማዋል እና/ወይም ማጠራቀም መቆጣጠር አንችልም፡፡
በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ ዉሰጥ “በእርስዎ የግል መረጃዎች ላይ እርስዎ ያለዎት መብት” የሚል ርዕስ ባለዉ ክፍል ዉስጥ እንደተብራራዉ፣ በዚያ ክፍል ዉስጥ እንደተገለጸዉ እኛ በእርስዎ ፒአይአይ ምን ማድረግ እንደምንችል እርስዎ ተዕጽኖ ማሳደር ይችላሉ፡፡

በእርስዎ የግል መረጃዎች ላይ እርስዎ ያለዎት መብት

የእነርሱን ፒአይአይ በሚመለከት የተጠቃሚዎች መብቶች የሚያካትቱት፡

  • የእነርሱን ፒአይአይ ቅጂዎች ማግኘት እና መቀበል፡፡
  • የእነርሱ ፒአይአይ እንዴት እንደተገኘ እና ጥቅም ላይ እንደዋለ መረዳት፡፡
  • የእነርሱ ፒአይአይ ላይ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ፡፡
  • እኛ የእነርሱን ፒአይአይ ጥቅም ላይ የምናዉልበትን መንገድ ማሻሻል፡፡

የእነዚህን መብቶች የትኛዉንም አገልግሎት ላይ ለማዋል፣ ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል፣ ማረጋገጥ የምንችለዉ የኢሜይል አድራሻ ማቅረብ አለባቸዉ እና ከዚህ በታች በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ ዉስጥ “እንዴት እኛን በመጠይቆች፣ አስተያየቶች፣ እና ጥያቄዎች አማካኝነት ማግኘት እንደሚቻል” የሚል ርዕስ ያለዉ ክፍል ዉስጥ የተጠቀሱትን መመሪያዎችን መከተል ያስፈልጋል፡፡ ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል፣ ማረጋገጥ የምንችለዉ የኢሜይል አድራሻ ማቅረብ ካልቻለሉ፣ እኛ ልናገኛቸዉ አንችልም፤ ይህም (1) እኛ በዚህ ፓሊሲ ላይ የሚደረጉ ለዉጦች እና/ወይም ከእነርሱ ፒአይአይ ጋር የሚያያዙ ችግሮች ለማሳወቅ (2) እና የእነርሱን ፒአይአይ ማግኘት፣ ማስተካከል፣ መቆጣጠር እና መሰረዝ መብታቸዉን መገልገል እንዲችሉ እኛ ማንነታቸዉን ለማረጋገጥ እንዳንችል ይገድበናል፡፡

የድርጅቱ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ግላዊነት ፓሊሲ እና ልምምዶች፡

እኛ እድሜያቸዉ ከ 13 ዓመት በታች ከሆኑ ግለሰቦች መረጃዎችን አስበንበት አንሰበስብም፣ የእኛ ስርዓት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ላይ ያተኮረ ስላልሆነ፣ የእኛን ዌብሳይት እና አገልግሎቶች በመየቀም የተጠቃሚዎችን እድሜ አናረጋግጥም፡፡ ይህ ማለት ሳናስብበት እና ባለማወቅ ስርዓቱን የሚጠቀም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የተወሰኑ ፒአይአይ ልንሰበስብ እንችል ይሆናል፡፡ እድሜያቸዉ ከ 13 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎችን ፒአይአይ ተጠቃሚዎች በሚያቀርቡበት ሁኔታ ላይ፣ ድርጅቱ ይህን መሰሉን ፒአይአይ በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ መሰረት የሚያያቸዉ ይሆናል፡፡ እኛ እያወቅን እድሜዉ ከ 13 ዓመት በታች ከሆነ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የምንፈጥር ከሆነ፣ እኛ ግለሰቦቹ ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የወላጆቻቸዉን ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባቸዉ መመሪያ እንሰጣቸዋለን፡፡

የመረጃ ደህንነት እና ይዞ ማቆየት ፓሊሲዎች እና ልምምዶች፡

የእርስዎን ፒአይአይ ደህንነት ለማረጋገጥ፣ እኛ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃዎች እንወስዳለን፡

  • ይህን ፓሊሲ የሚመለከት ትምህርት፡ እኛ ለሰራተኞቻችን፣ ተባባሪዎች፣ እና ሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች የዚህን ግላዊነት ፓሊሲ ዝርዝሮች የሚመለከት ትምህርት በንቃት እንሰጣለን፣ በዚህም በእነርሱ ጥበቃ ስር የሚገኝን ፒአይአይ ባልተፈቀደ መልኩ ማግኘት ወይም ጥቅም ላይ ማዋልን ለመከላከል የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና እንዲገነዘቡ አጠንክረን እናስተምራለን፡፡
  • የደህንነት ማሻሻያዎች፡ የእኛ ቀጣይነት ያለዉ የፒአይአይ ደህንነትን የማሻሻል ቁርጠኛ ፍላጎት በእኛ ወቅታዊ ጥረቶች መመልከት ይቻላል፡፡ እኛ ቀደም ብለን ባልተፈቀደ መልኩ ፒአይአይ ማግኘት ወይም ያለ አግባብ መጠቀም ሁኔታን ለማስቀረት በርካታ የደህንነት ፕሮቶኮሎች ስራ ላይ እንዲዉሉ አድርገናል፡፡ የእኛን የደህንነት ደረጃ ከፍ የማድረግ ተነሳሽነት ሂደትን ካጠናቀቅን በኋላ፣ ስለ እነዚህ እርምጃዎች የዘመነ አጠቃላይ እይታ በዚህ ግላዊነት ፓሊሲ ዉስጥ የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ለማንኛዉም ማብራሪያ ጥያቂዎች እኛን ለማግኘት እርስዎ ነጻነት ይሰማዎት፡፡
  • መረጃ ይዞ መቆየት ፓሊሲ፡ በመደበኝነት፣ የእኛ ልምምድ ከተሰበሰበ አንድ ዓመት የሞላዉን ፒአይአይ መሰረዝ ነዉ፡፡ ቢሆንም ግን፣ የእኛ ስርዓት ያለዉን ዉስብስብነት ግምት ዉስጥ በማስገባት፣ ይህ በዚህ ጊዜ መጠን ዉስጥ ይህን ማድረግ ሁልጊዜ ላይሳካ ይችላል፡፡ ይህ ይዞ መቆየት ፓሊሲ በሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች ለተሰበሰበ ወይም ለተጠራቀመ ፒአይአይ ላይ ተግባራዊ እንደማይሆነ ልብ ብለን ማስተዋላችን ጠቃሚ ነዉ፡፡
  • የመረጃ ኢንክሪፕሽን ፓሊሲ፡ የተሰበሰበ ፒአይአይ ኢንክሪፕት የማድረግ ወሳኝነት እዉቅና በመስጠት፣ እኛ ሁሉም ፒአይአይ ሙሉ በሙሉ ኢንክሪፕት መደረጉን ለማረጋገጥ የእኛ ስርዓት ላይ በንቃት ማሻሻያ እያደረግን እንገኛለን፡፡ በአሁኑ ወቅት፣ ይህ ሂደት በሁሉም ፒአይአይ ዙሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ ይህ የኢንክሪፕሽን ስትራቴጂ በሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች ስር የሚገኝን ፒአይአይ አያጠቃልልም፡፡
  • ሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች፡ ሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎችን በሚመለከት፣ እኛ እነርሱ አለን ብለዉ የሚገልጹትን የደህንነት እርምጃዎች ለማረጋገጥ ገለልተኛ የሆነ ማረጋገጫ አላደረግንም፡፡ ይህን መሰሉ ገለልተኛ ግምገማ ማድረግ ለእኛ አይነት ድርጅት እጅግ በጣም የገንዘብ ወጪ የሚጠይቅ እና ጊዜ የሚወስድ ሂደት ነዉ፤ እና አብዛኞቹ ሶስተኛ- ወገን አገልግሎት አቅራቢዎች ይህን መሰሉ ግምገማዎች እንዲካሄዱ አይፈቅዱም፡፡

“ክትትል አታድርግ” ይፋ ማድረጊያ፡

እኛ ተጠቃሚዎችን ዒላማ የሚያደርጉ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ በሶስተኛ- ወገን ዌብሳይቶች ዙሪያ ሰዎች ላይ ክትትል አናደርግም፡፡ ስለሆነም፣ እኛ ክትትል አታድርግ (ዲኤንቲ) ምልክቶች ምላሽ አንሰጥም፡፡

እንዴት እኛን በመጠይቆች፣ አስተያየቶች፣ እና ጥያቄዎች አማካኝነት ማግኘት እንደሚቻል፡

እርስዎ ለሚኖርዎት መጠይቆች፣ አስተያየቶች፣ ወይም ጥያቄዎች፣ በ info@howtouseabortionpill.org አድራሻ ኢሜይል ይላኩልን፡፡ እኛ ፒአይአይ የሚመለከት ዉይይት ከማድረጋችን በፊት በመዝገባችን- ዉስጥ የሚገኘዉን የኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ማንነትን እናረጋግጣለን፡፡
ከላይ እንደተገለጸዉ፣ ተጠቃሚዎች በመጀመሪያ ከእኛ ጋር ግንኙነት ከመፍጠራቸዉ እና ፒአይአይ ለእኛ ማቅረብ ከመጀመራቸዉ በፊት አገልግሎት የሚሰጥ፣ ማረጋገጥ የሚቻል የኢሜይል አድራሻ የማያቀርቡ ከሆነ፣ እኛ በቀጣይነት የእነርሱን ማንነት ማረጋገጥ አንችልም፤ እና ይህም ሁኔታ በእኛ ስር የሚገኝ ፒአይአይ ጋር ተያያዥነት ያለዉ ምንም አይነት መብቶችን ማንም ሰዉ መገልገል እንዲችል ፈቃድ እንዳንሰጥ ይከለክለናል፡፡

በመጨረሻ የዘመነዉ፡

ይህ የግላዊነት ፓሊሲ የዘመነዉ በፌብሩዋሪ 14፣ 2024 ነበር፡፡ እና ይህን የግላዊነት ፓሊሲ በእያንዳንዱ 12 ወራቶች ቢያንስ አንድ ጊዜ የምናዘምን ይሆናል፡፡

 

HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org መሰረቱን በዩኤስ ካደረገ በ501c(3) ስር ከተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ጋር በሽርክና ይሰራል።
HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org provides ይዘትን ላይ የተመሰረተ መረጃ ለመረጃነት አላማዎች እንዲያገለግል ብቻ የሚያቀርብ ከመሆኑ በቀር ከህክምና ድርጅት ጋር በሽርክና አይሰራም።

    የተጎላበተው በ Women First Digital