እንክብሎችን በመጠቀም ጽንስ ማስወረድ እንዴት እንደሚሰራ
ሚፈፕሪስቶን ጽንሱ እድገቱን እንዳይቀጥል ያስቆመዋል፣ እና የማህጸን ጫፍ(ወደ ማህጸን ማስገቢያ) እንዲከፈት ይረዳል፡፡ ሚሶፕሮስቶል ማህጸን እንዲኮማተር ያደርጋል፣ ይህም በስተመጨረሻ እርግዝናዉ እንዲገፋ ያደርጋል፡፡
ሚሶፕሮስቶል ወደ ሰዉነት እንዲሰራጭ ከተደረገ በኋላ፣ ቁርጠት እና የደም መፍሰስ የሚጀምሩ ይሆናል፡፡ ይህም በአብዛኛዉ ጊዜ ላይ የመጀመሪያዎቹ እንክብሎች ስብስብ ከተወሰዱ በኋላ በሚኖሩት 1 እስከ 2 ሰዓታት ዉስጥ የሚጀምር ይሆናል፡፡ የጽንስ ማስወረዱ ሂደት አብዛኛዉ ጊዜ ላይ የመጨረሻዎቹ የሚሶፕሮስቶል እንክብሎች ከተወሰደ በኋላ በሚኖሩት 24 ሰዓታቶች ዉስጥ የሚከሰት ይሆናል፡፡ በአብዛኛዉ ጊዜ ላይ፣ ይህ ሂደት ከዚህ ጊዜ ቆይታ በፊትም የሚከሰት ይሆናል፡፡
ስጋት ከያዘሽ
ከዚህ በታች የተገለጹት መንገዶች የጽንስ ማስወረድ ሂደቱ ስኬታማ መሆኑን ለይቶ ለማወቅ ይረዳሉ፡፡
- አንቺ የእርግዝና ሽሉ ሲወርድ ስሜቱን ለይተሸ ልታዉቂዉ ትችያለሽሽ፡ ይህም ጥቁር መልክ ያለዉ ቀጭን ሽፋን የለበሱ የረጋ ደም፣ ወይም በነጭ፣ ለስላሳ ሽፋን የተከበበ ትንሽ ከረጢት ሊመስል ይችላል፡፡ በጽንሱ እድሜ ላይ በመመስረት፣ ከአንቺ የጣት ጥፍር ያነሰ፣ ወይም አዉራ ጣትሽን ዉፍረት ሊያክል ይችላል፡፡
- በጽንስ ማስወረድ ሂደት ላይ የሚከሰተዉ የደም መፍሰስ አብዛኛዉን ጊዜ ላይ ከወር አበባ ጋር ተመሳሳይ ነዉ፣ ወይም ከዚያም የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡
- የአንቺ የእርግዝና ምልክቶች መሻሻል ያሳያል፡፡ እንደ ጡት ሕመም፣ ማስመለስ፣ እና ድካም ህመሞች መሻሻል ማሳየት መጀመር አለባቸዉ፡፡
ዋቢዎች፦
- “Induced Abortion.” American College of Obstetrics and Gynecologists.
https://www.acog.org/Patients/FAQs/Induced-Abortion - “Care for Women Choosing Medication Abortion.” The Nurse Practitioner.
https://journals.lww.com/tnpj/Citation/2004/10000/Care_for_Women_Choosing_Medication_Abortion.9.aspx - “Safe abortion: technical and policy guidance for health systems.”The World Health Organization.
https://apps.who.int/iris/bitstream/handle/10665/70914/?sequence=1